ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ምሳሌውን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
ዘፀአት 27:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሌዳውም ፍልፍል ይሁን፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠዊያውን ውስጡን ባዶ ከሆኑ ሳንቃዎች አብጀው፤ ልክ በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ይበጅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሳንቃዎች ሠርተህ ባዶ አድርገው፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ ይሥሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሠዊያውን ከሳንቃዎች ሥራ፤ ውስጡም ባዶ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሳንቆች ሠርተህ ባዶ አድርገው፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ ያድርጉት። |
ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ምሳሌውን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
ዕውቀት እንደ ተሰጠው የእግዚአብሔርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈውን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ፤ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ” ብሎት ነበርና።