ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እንዲሁ አድርግ።
ዘፀአት 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀለበቶችን ትይዩ በማድረግ ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው ጠርዝ መጋረጃ፣ ዐምሳ ቀለበቶችንም በሌላው ጠርዝ መጋረጃ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት እንዲሆኑ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያው መጋረጃ መጀመሪያ ክፍል ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሁለተኛው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ላይ ከሌሎቹ ቀለበቶች ፊት ለፊት ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ። |
ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እንዲሁ አድርግ።
አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ።