እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ገበታውን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ ከመጋረጃው ውጭ በድንኳኑ በመስዕ በኩል አኖረው፤
ዘፀአት 26:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገበታውንም በመጋረጃው ውጭ፥ መቅረዙንም በገበታው ፊት ለፊት በድንኳኑ በደቡብ ወገን አድርግ፤ ገበታውንም በድንኳኑ በሰሜን ወገን አድርገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠረጴዛውን ከመገናኛው ድንኳን በሰሜን በኩል ከመጋረጃው ውስጥ አስቀምጠው፤ መቅረዙንም ከርሱ ትይዩ በማድረግ በደቡብ በኩል አድርገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገበታውንም በመጋረጃው ውጭ፥ መቅረዙንም በገበታው ፊት ለፊት በማደሪያው በደቡብ ወገን አድርግ፤ ገበታውንም በሰሜን ወገን አድርገው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠረጴዛውን ከቅድስተ ቅዱሳኑ ውጪ፥ ከድንኳኑ በስተ ሰሜን በኩል አኑር፤ መቅረዙንም በደቡብ በኩል አኑር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገበታውንም በመጋረጃው ውጭ፥ መቅረዙንም በገበታው ፊት ለፊት በማደሪያው በደቡብ ወገን አድርግ፤ ገበታውንም በሰሜን ወገን አድርገው። |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ገበታውን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ ከመጋረጃው ውጭ በድንኳኑ በመስዕ በኩል አኖረው፤
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው መቅረዙን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በገበታውም ፊት ለፊት፥ በድንኳኑ በአዜብ በኩል አኖረ፤
የመጀመሪያዪቱም ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበረባት።