ዘፀአት 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎችም አምስት መጋረጃዎች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ።። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስቱን መጋረጃዎች አገጣጥመህ ስፋ፤ የቀሩትንም ዐምስት መጋረጃዎች እንደዚሁ አገጣጥመህ ስፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስቱ መጋረጆች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ አምስቱም መጋረጆች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎቹም አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው በመገጣጠም ተሰፍተው በሌላ በኩል ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስቱ መጋረጆች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ አምስቱም መጋረጆች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ። |
ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እንዲሁ አድርግ።
አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስቱም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስተኛውም መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ይደረብ።
አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንዱን ከሌላው ጋር አጋጠሙ፤ አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው እንዲሁ አጋጠሙ።
ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ አብ በእኔ እንዳለህ፥ እኔም በአንተ እንዳለሁ፥ እነርሱም እንደ እኛ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ።
ከእርሱ የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠው በሥር ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚኖርበት፥ በሥርና በጅማትም በሚስማማበት፥ በእግዚአብሔርም በሚያድግበትና በሚጸናበት፥ በሚሞላበትም በራስ አይጸናም።
ይኸውም ልቡናቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትምህርታቸውም በማወቅ፥ በፍቅርና ፍጹምነት ባለው ባለጸግነት፥ በጥበብና በሃይማኖት፥ ስለ ክርስቶስም የሆነውን የእግዚአብሔርን ምክር በማወቅ ይጸና ዘንድ ነው።