አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ።
ዘፀአት 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውጭ ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ እንዲሁም በሌላ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንድ በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሌላም በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። |
አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ።
ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እንዲሁ አድርግ።
አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስቱም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ ሆነው ይጋጠሙ፤ ስድስተኛውም መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ይደረብ።
አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ።