ዘፀአት 15:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንን ሰረገሎች፥ ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው። በሦስት የተከፈሉ ፈረሰኞችም በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈርዖንን ሠረገሎችና ሰራዊት፣ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ ምርጥ የሆኑት የፈርዖን ሹማምት፣ ቀይ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንን ሰረገሎችና ሠራዊቱን በባሕር ጣላቸው፤ የተመረጡት መኮንኖችም በቀይ ባሕር ሰጠሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የንጉሡን ሠራዊት ከነሠረገላው ወደ ባሕር ጣለ፤ ምርጥ የሆኑት የጦር አዛዦች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰጥመው ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው፤ የተመረጡት ሦስተኞች በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ። |
ማርያምም አስቀድማ ለእግዚአብሔር እንዘምር አለች፥ “ለእግዚአብሔር እንዘምር በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጥሎአልና።”