አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽም ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ በሩቁ እንደምትታይ እንደ ማኅበር ማሕሌት ናት።
ኤፌሶን 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰላም ወንጌል ኀይልንም ተጫምታችሁ ቁሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰላም ወንጌል ለማወጅ በዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰላምን ወንጌል እንደ ጫማ በእግሮቻችሁ ተጫምታችሁ በመዘጋጀት ቁሙ። |
አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽም ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ በሩቁ እንደምትታይ እንደ ማኅበር ማሕሌት ናት።
ሰላምን የሚያወራ፥ መልካም የምሥራችንም የሚናገር፥ መድኀኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፥ “አምላክሽ ነግሦአል” የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ያማሩ ልብሶችን ቶሎ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱም ቀለበት፥ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤’