በዚያም ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ በሁለት ተከፈለ፤ የሕዝቡም እኩሌታ የጎናትን ልጅ ታምኒን ያነግሡት ዘንድ ተከተሉት፤ እኩሌቶችም ዘንበሪን ተከተሉ።
ኤፌሶን 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድ መንፈስና በሰላም ማሰሪያነት እየተጠበቃችሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰላም ተሳስራችሁ ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚገኘውን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። |
በዚያም ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ በሁለት ተከፈለ፤ የሕዝቡም እኩሌታ የጎናትን ልጅ ታምኒን ያነግሡት ዘንድ ተከተሉት፤ እኩሌቶችም ዘንበሪን ተከተሉ።
ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት፤ እንዳይቀደድም በግብረ መርፌ የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
ወድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ደስ ይበላችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአንድ ልብም ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የሰላምና የፍቅር አምላክም ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ አንድ እስክንሆን ድረስ በክርስቶስ ምልዐት መጠን፥ አካለ መጠን እንደ አደረሰ እንደ አንድ ሙሉ ሰው እስክንሆን ድረስ፥