ከእኔ ጋር ካሉ ከቅዱሳን መላእክት አንዱን ጠየቅሁት፥ እንዲህም አልሁት- “ይህ የሚያበራው ምንድን ነው? ሰማይ አይደለምና፥ ነገር ግን ብቻውን የሚነድድ የእሳት ወላፈን፥ የጩኸትና የልቅሶ፥ የዋይታና የብርቱ ሕማም ቃል ነው።”