እኔም ሄኖክ ስለ እርሱ መለስሁ፥ እንዲህም አልሁት- “እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገርን ያደርጋል፤ የአባቴ የያሬድ የልጁ ወገኖች ከሰማይ በላይ ያለ የጌታን ቃል ተላልፈዋልና ይህን በራእይ ፈጽሜ አይቼ ነገርሁህ።