ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓይንም ማየት ለዐይን መልካም ነው።
ብርሃን መልካም ነው፤ ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል።
ብርሃን ጣፋጭ ነው ፀሐይንም ማየት ለዐይን መልካም ነው።
ብርሃን ታይቶ አይጠገብም፤ ስለዚህ የቀንን ብርሃን እያዩ መደሰት መልካም ነው።
ብርሃን ጣፋጭ ነው ፀሐይንም ማየት ለዓይን መልካም ነው።
ነፍሴ ወደ ጥፋት እንዳትወርድ አድኖአታል፥ ሕይወቴም ብርሃንን ታያለች።’
ሕይወቴም በብርሃን ውስጥ ታመሰግን ዘንድ፥ እርሱ ነፍሴን ከሞት አድኖአታል።
ቅንነት ከምድር በቀለች፥ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተ።
መልካምን ነገር የሚያይ ዐይን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ዜናም አጥንትን ያለመልማል።
ፀሓይና ብርሃን፥ ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፥
ደግሞም ፀሐይን አላየም፥ አላወቀምም፤ ስለዚህ ከዚያ ይልቅ ለዚህ ዕረፍት አለው።
ጥበብ ከርስት ጋር መልካም ነው፤ ፀሓይንም ለሚያዩ ሰዎች ትርፍን ይሰጣል።