መክብብ 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢብ ልብ በስተቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተግራው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተ ግራው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኛ መልካም ነገር መሥራቱ፥ ሞኝም መሳሳቱ የተለመደ ተግባር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተ ግራው ነው። |
ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።
ምሣሩ ከዛቢያው ቢወልቅ ሰውየው ፊቱን ወዲያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይልም ያስፈልገዋል። ጥበብ ግን ለብርቱ ሰው ትርፉ ነው፤
ሰነፍ ነገርን ያበዛል፤ ሰውም የሆነውንና ወደ ፊት የሚሆነውን አያውቅም፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ይነግረዋል?
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።