ዘዳግም 4:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአርኖን ወንዝ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ ኤርሞን ድረስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሴዎን ተራራ ማለትም እስከ አርሞንዔም የሚደርስ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአርኖን ወንዝ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ እስከ ሲሪዮን ተራራ፥ ይህም ሔርሞን ድረስ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ምድር ከዓሮዔር ከተማ በመነሣት በአርኖን ወንዝ ጫፍ አልፎ በሰሜን በኩል እስከ ሢርዮን ተራራ የሚደርስ ነው፤ ይህም የሢርዮን ተራራ ተብሎ የሚጠራው የሔርሞን ተራራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአርኖን ወንዝ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ እስከ ሲዎን ተራራ እስከ አርሞንዔም ድረስ፥ |
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን።
“ይህችንም ምድር በዚያን ዘመን ወረስን፤ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ ሀገር እኩሌታ፥ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገድ ሰጠኋቸው።
“በዚያም ዘመን ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ኤርሞን ድረስ ምድሪቱን በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞሬዎን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤