ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
ዘዳግም 4:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ሙሴ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞችን ለየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሙሴ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞች በመለየት ከለለ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ በስተምሥራቅ ሦስት ከተሞች በመለየት ከለለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ሙሴ ትናንት ከትናንት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይሸሽባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች ለየ። |
ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር፤ በምትካፈላት ርስትህ አባቶችህ የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።
ትናንት፥ ከትናት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይማፀንባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ተማፅኖ በሕይወት ይኖር ዘንድ፤