ነገር ግን ኮረብታዎች ገና በዚያ ነበሩ፤ ሕዝቡም ገና ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር አላቀኑም ነበር።
ዘዳግም 29:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖቻችሁም ያዩአቸውን ታላላቆች ፈተናዎችን፥ ታላላቆች ተአምራትንና ድንቆችን አይታችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚያን ከባድ ፈተናዎች፣ ታምራዊ ምልክቶችና ታላላቅ ድንቆች በገዛ ዐይኖቻችሁ አይታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖቻችሁ ከባድ ፈተናዎችን፥ ታምራዊ ምልክቶችንና ታላላቅ ድንቆች አይተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱ ላይ ያደረሰባቸውን አሠቃቂ መቅሠፍት፥ የፈጸመውንም ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖቻችሁ ያዩአቸውን ታላላቆች ፈተናዎች፥ ታላላቆች ተአምራትና ድንቆች፥ አይታችኋል፤ |
ነገር ግን ኮረብታዎች ገና በዚያ ነበሩ፤ ሕዝቡም ገና ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር አላቀኑም ነበር።
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
“የሰው ልጅ ሆይ! በዐመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፤ እነርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፤ ይሰሙም ዘንድ ጆሮ አላቸው፤ ነገር ግን አይሰሙም፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ጠርቶ አላቸው፥ “እግዚአብሔር በፊታችሁ በግብፅ ምድር፥ በፈርዖንና በሹሞቹ ሁሉ፥ በምድሩም ሁሉ ያደረገውን ሁሉ፥