ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳዪቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ‘ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔም ጋር ሊኖር አልወደደም’ ትበላቸው።
ዘዳግም 25:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማውም ሽማግሌዎች ጠርተው ይጠይቁት፤ እርሱም በዚያ ቆሞ፦ ‘አገባት ዘንድ አልወድድም’ ቢል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ያን ሰው ጠርተው ያነጋግሩት፤ እርሱም፣ “እርሷን ላገባት አልፈልግም” ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ሰው ጠርተው ያነጋግሩት፤ እርሱም፥ ‘እርሷን ላገባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የከተማይቱ መሪዎች ሰውየውን ጠርተው ያነጋግሩት፤ አሁንም እርስዋን ለማግባት ፈቃደኛ ባይሆን መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማውም ሽማግሌዎች ጠርተው ይጠይቁት፤ እርሱም በዚያ ቆሞ፦ አገባት ዘንድ አልወድድም ቢል፥ |
ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳዪቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ‘ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔም ጋር ሊኖር አልወደደም’ ትበላቸው።
ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።
እኔም በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት እንድትገዛው አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ። መቤዠት ብትወድድ ተቤዥው፣ መቤዥት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከእንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም፦ እቤዥዋለሁ አለው።
በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤል ምስክር ነበረ።