በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ መስፈሪያ አይኑርልህ።
በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩህ።
በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ።
“በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ ሚዛን አይኑርልህ።
አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ።