በውኑ እና መልካም ነገር እናገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እናድርግ እንደምንል አስመስለው የሚጠረጥሩንና የሚነቅፉን ሰዎች እንደሚሰድቡን ነን? ለእነርሱስ ቅጣታቸው ተዘጋጅቶላቸዋል።
ዘዳግም 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሰው ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ሁለቱን የብልቱን ፍሬዎች ብትይዝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፣ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ፣ እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፥ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ፥ እጅዋን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሁለት ሰዎች ተጣልተው በሚተናነቁበት ጊዜ የአንደኛው ሚስት ባልዋን ለማገዝ የሌላውን ሰው ብልት ብትጨብጥ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ፥ |
በውኑ እና መልካም ነገር እናገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እናድርግ እንደምንል አስመስለው የሚጠረጥሩንና የሚነቅፉን ሰዎች እንደሚሰድቡን ነን? ለእነርሱስ ቅጣታቸው ተዘጋጅቶላቸዋል።
እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።