La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሰ​ደ​ዳት የቀ​ድሞ ባልዋ ከረ​ከ​ሰች በኋላ ደግሞ ያገ​ባት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤ ያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠላ ነውና፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር አታ​ር​ክስ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፣ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኀጢአት አታምጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሁለቱም መንገድ ቢሆን ያ የመጀመሪያ ባልዋ እንደገና ሊያገባት አይፈቀድለትም፤ እንደ ረከሰች አድርጎ ይቊጠራት፤ እርስዋን እንደገና ቢያገባ ይህ ድርጊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ስትኖሩ እንደዚህ ያለውን አስከፊ ኃጢአት መፈጸም አይገባችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 24:4
6 Referencias Cruzadas  

“ሰው ሚስ​ቱን ቢፈታ፥ ከእ​ር​ሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመ​ለ​ሳ​ለ​ችን? ያች ሴት እጅግ የረ​ከ​ሰች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? አን​ቺም ከብዙ እረ​ኞች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ወደ እኔም ትመ​ለ​ሻ​ለ​ሽን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ባል ቢጠ​ላት፥ የፍ​ች​ዋ​ንም ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ቢሰ​ጣት ፥ ከቤ​ቱም ቢሰ​ድ​ዳት፥ ወይም ሚስት አድ​ርጎ ያገ​ባት ሁለ​ተ​ኛው ባልዋ ቢሞት፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ።