ዘዳግም 22:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና፥ የሚታደጋትም አልነበረምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ማንም ሰው ስላልነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ብትጮህም የሚደርስላት አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚሆንበት ምክንያት ያ ሰው ያቺን ለሌላ ሰው ታጭታ የነበረች ልጃገረድ ከከተማ ውጪ በዋለችበት አግኝቶአት ስለ ነበርና ርዳታ ለማግኘት ብትጮኽም የሚደርስላት በማጣትዋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና የሚታደጋትም አልነበረምና። |
በብላቴናዪቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉ፤ በብላቴናዪቱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ኀጢአት የለባትም፤ ሰው በባልንጀራው ላይ ተነሥቶ እንደሚገድለው ይህ ነገር ደግሞ እንደዚሁ ነውና፤