ዘዳግም 20:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስትም አጭቶ ያላገባት ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያገባት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ አለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስት ለማግባትስ ልጃገረድ ያጨ ሰው አለን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት እርሱ ያጫት ልጃገረድ ለሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስትም አጭቶ ያላገባትም ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያገባት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። |
ወይንም ተክሎ ደስ ያልተሰኘበት ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው ደስ እንዳይሰኝበት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።
“አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሂድ፤ ምንም ነገር አይጫኑበት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈቃዱ ይቀመጥ፤ የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት።
ሚስት ታገባለህ፤ ሌላም ሰው ይነጥቅሃል፤ ቤት ትሠራለህ፤ በእርሱም አትቀመጥበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ከእርሱም አትለቅምም።