La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወይ​ንም ተክሎ ደስ ያል​ተ​ሰ​ኘ​በት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው ደስ እን​ዳ​ይ​ሰ​ኝ​በት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ወይኑን ሌላ ሰው ይበላዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ወይኑን ሌላ ሰው ይበላዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወይስ አዲስ የወይን ተክል ተክሎ የመጀመሪያውን ፍሬ ያልሰበሰበ ሰው ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ወይን ጠጁ ለሌላ ሰው መደሰቻ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወይንም ተክሎ ፍሬውንም ያልበላ ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው ፍሬውን እንዳይበላ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 20:6
8 Referencias Cruzadas  

ሌላ እን​ዲ​ቀ​መ​ጥ​በት አይ​ሠ​ሩም፤ ሌላም እን​ዲ​በ​ላው አይ​ተ​ክ​ሉም፤ የሕ​ዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይ​ወት ዛፍ ዕድሜ ይሆ​ና​ልና፥ እኔም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


እንደ ገናም በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ የወ​ይን ተክ​ሎ​ችን ትተ​ክ​ሊ​አ​ለሽ፤ የም​ት​ተ​ክሉ ትከሉ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤


ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።


የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም ምግ​ቡን ያገኝ ዘንድ ነው፤ ወይን ተክሎ ፍሬ​ውን የማ​ይ​በላ ማን ነው? መን​ጋ​ው​ንስ ጠብቆ ወተ​ቱን የማ​ይ​ጠጣ ማን ነው?


ጸሐ​ፍ​ትም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላ​ስ​መ​ረቀ ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ስ​መ​ር​ቀው ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።


ሚስ​ትም አጭቶ ያላ​ገ​ባት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ገ​ባት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።