ዘዳግም 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምድረ በዳው አንሥቶ እዚህ እስከምትደርሱ ድረስ፣ ለእናንተ ያደረገላችሁን ያዩት ልጆቻችሁ አልነበሩም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድረ በዳው አንሥቶ እዚህ እስከምትደርሱ ድረስ፥ ለእናንተ ያደረገላችሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚህ ከመድረሳችሁም በፊት እግዚአብሔር በዚያ በረሓ ምን እንዳደረገ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥ |
በተከተሉአችሁም ጊዜ በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ በግብፅ ጭፍራ በፈረሶቻቸውም፥ በሰረገሎቻቸውም ያደረገውን፥
በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንም፥ ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ሁሉ፤