ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮረብታው ላይ ይሠዋና ያጥን ነበር።
ዘዳግም 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዐት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም እንዲሆንልህና ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞችና የእግዚአብሔር ሥርዐቶች እንድትጠብቅ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት እንድትጠብቅ ነው። |
ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮረብታው ላይ ይሠዋና ያጥን ነበር።
ልጄ ሆይ፥ ለራስህ ጠቢብ ብትሆን ለባልንጀራህም ጠቢብ ትሆናለህ፥ ክፉም ብትሆን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ይመስላል። እርሱም የሚበርር ዎፍን እንደሚከተል ነው። የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤ የሚሰማራባትን መንገድ ዘነጋ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች ምድርም ይሄዳል፤ የማያፈራና የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዐት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን።