ንጉሡም ያመልከው ነበር፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ እየሄደ ይሰግድለት ነበር፤ ዳንኤል ግን ለፈጣሪው ይሰግድ ነበር። ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ለቤል የማትሰግድ ለምንድን ነው?” አለው።