ዳግመኛም ቀልጦ የተሠራውን እንቦሳ አድርገው፦ ‘ከግብፅ ያወጡን አምላኮቻችን እሊህ ናቸው’ አሉ፤ እጅግም አስቈጡህ፤
አሞጽ 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል ቤት ሆይ! በውኑ በምድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኛልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል ቤት ሆይ! በውኑ አርባ ዓመት በምድረ በዳ መሥዋዕትንና ቁርባንን አቅርባችሁልኛልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በውኑ በአርባው ዓመት የምድረ በዳው ጒዞ ጊዜ መሥዋዕትና መባ አቅርባችሁልኛልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ በምድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኛልን? |
ዳግመኛም ቀልጦ የተሠራውን እንቦሳ አድርገው፦ ‘ከግብፅ ያወጡን አምላኮቻችን እሊህ ናቸው’ አሉ፤ እጅግም አስቈጡህ፤
ፍርዴን አላደረጉምና፥ ሥርዐቴንም ጥሰዋልና፥ ሰንበታቴንም አርክሰዋልና፥ ዐይኖቻቸውም የአባቶቻቸውን ዐሳብ ተከትለዋልና።
እነርሱ ግን ዐመፁብኝ፤ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ርኵሰቱን ከፊቱ አላስወገደም፤ የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ በግብፅ ምድር መካከል ቍጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
መሥዋዕታቸውንም ደግሞ ተከትለው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት አይሠዉ። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።”
ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
“አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩት፤ በእውነትና በቅንነትም አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ፥ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን ሌሎች አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ።