የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ የድኅነት መሥዋዕታችሁንም አልመለከትም።
አሞጽ 5:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላዳምጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዝማሬህን ጩኸት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ዜማ አልሰማም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ዜማ አላዳምጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመዝሙራችሁን ጩኸት ከእኔ አርቁ፤ የበገናችሁንም ዜማ መስማት አልፈልግም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፥ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። |
የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ የድኅነት መሥዋዕታችሁንም አልመለከትም።
ከበገናው ድምፅ ጋር አስተባብረው ለሚያጨበጭቡ ሰዎች፤ ይኸውም የማያልፍ ለሚመስላቸውና እንደሚያመልጣቸው ለማያውቁ፤
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
ያንጊዜም በመቅደሶቻቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በየስፍራው የሚወድቀው ሬሳ ይበዛልና፤ እነርሱም ይጠፋሉና።