እርሱም፥ “ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? አሁንም ወርቁንና ልብሱን፥ ተቀብለሃል፤ ለወይን ቦታ፥ ለመሰማርያ ቦታና ለዘይት ቦታ፥ ለላሞችና ለበጎች፥ ለወንዶችና ለሴቶች ባሮች ይሁንህ።
ሐዋርያት ሥራ 8:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጃንደረባውም፥ “ያስተማረኝ ሳይኖር በምን አውቀዋለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረገላውም ወጥቶ አብሮት ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጃንደረባውም፣ “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” አለው፤ እርሱም ወደ ሠረገላው ወጥቶ ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢትዮጵያዊውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ሊገባኝ ይችላል?” አለና ፊልጶስን “ወደ ሠረገላው ውጣና ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። |
እርሱም፥ “ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? አሁንም ወርቁንና ልብሱን፥ ተቀብለሃል፤ ለወይን ቦታ፥ ለመሰማርያ ቦታና ለዘይት ቦታ፥ ለላሞችና ለበጎች፥ ለወንዶችና ለሴቶች ባሮች ይሁንህ።
በዚያም ንጹሕ መንገድ ይሆናል፤ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ በዚያም ንጹሓን ያልሆኑ አያልፉበትም፤ ርኩስ መንገድም በዚያ አይኖርም፤ የተበተኑትም በእርሱ ይሄዳሉ፤ አይሳሳቱምም።
ፊልጶስም ፈጥኖ ደርሶ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማው፤ ፊልጶስም፥ “በውኑ የምታነበውን ታውቀዋለህን?” አለው።
ያነበው የነበረ የመጽሐፉ ቃልም እንዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
ራሳችሁን አታስቱ፤ ከመካከላችሁ በዚህ ዓለም ጥበበኛ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላዋቂ ያድርግ።