ሙሴ በተወለደ ጊዜ በእምነት ሦስት ወር በአባቱ ቤት ሸሸጉት፤ ሕፃኑ መልካም እንደ ሆነ አይተውታልና፤ የንጉሥንም ትእዛዝ አልፈሩም።
ሐዋርያት ሥራ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ያንጊዜም ሙሴ ተወለደ፤ በእግዚአብሔር ፊትም የተወደደ ሆነ፤ ለሦስት ወርም በአባቱ ቤት አሳደጉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚህ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘ ውብ ሕፃን ነበር። በአባቱም ቤት ሦስት ወር በእንክብካቤ አደገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ሕፃን ነበር፤ ሦስት ወር በአባቱ ቤት አደገ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ በእግዚአብሔርም ፊት ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ፤ |
ሙሴ በተወለደ ጊዜ በእምነት ሦስት ወር በአባቱ ቤት ሸሸጉት፤ ሕፃኑ መልካም እንደ ሆነ አይተውታልና፤ የንጉሥንም ትእዛዝ አልፈሩም።
ልኮም አስመጣው፤ እርሱም ቀይ፥ ዐይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ይህ መልካም ነውና ተነሥተህ ዳዊትን ቅባው” አለው።