ሐዋርያት ሥራ 25:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበደሉ ደብዳቤ ሳይኖር እስረኛን ወደ ንጉሥ መላክ አይገባምና፤ ለእኔም ነገሩም ሆነ አስሮ መላኩ አስቸግሮኛል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም አንድ እስረኛ ወደ በላይ ሲላክ የተከሰሰበትን ምክንያት አለመግለጽ ትክክል ስላልመሰለኝ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስረኛ ሲላክ የተከሰሰበትን ምክንያት ደግሞ አለማመልከት ሞኝነት መስሎኛልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስረኛ ወደ በላይ ሲላክ፥ የተከሰሰበትን ምክንያት አለመግለጥ ሞኝነት መስሎ ታይቶኛል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስረኛ ሲላክ የተከሰሰበትን ምክንያት ደግሞ አለማመልከት ሞኝነት መስሎኛልና።” |
ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የምጽፈው የታወቀ ነገር የለኝም። ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን አገኝ ዘንድ ወደ እናንተ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመጣሁት።
አግሪጳም ጳውሎስን፥ “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ፈቅደንልሃል” አለው፤ ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጁን አነሣና ይነግራቸው ጀመር፤ እንዲህም አለ፦