ሐዋርያት ሥራ 25:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ክርክራቸውም የማደርገውን አጥቼ ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ በዚያ ልትከራከር ትወዳለህን? አልሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ይህን ነገር እንዴት እንደምፈታው ግራ ስለ ገባኝ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ስለዚሁ ጕዳይ እንዲፋረድ ፈቃደኛነቱን ጠየቅሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ይህን ነገር እንዴት እንድመረምር አመንትቼ ‘ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ በዚህ ነገር ከዚያ ልትፋረድ ትወዳለህን?’ አልሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እንዲህ ዐይነቱን ነገር መመርመር ስለ ቸገረኝ ጳውሎስን ‘ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ እዚያ በዚህ ነገር ልትፋረድ ትወዳለህን?’ አልኩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ይህን ነገር እንዴት እንድመረምር አመንትቼ፦ “ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ በዚህ ነገር ከዚያ ልትፋረድ ትወዳለህን?” አልሁት። |
ፊስጦስ ግን አይሁድ እንዲያመሰግኑት ወዶ ጳውሎስን፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ነገር በዚያ ከእኔ ዘንድ ልትከራከር ትሻለህን?” አለው።