ሐዋርያት ሥራ 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገቡ ቆመው የነበሩትም ጳውሎስን፥ “እግዚአብሔር የሾመውን ሊቀ ካህናት እንዴት ትሳደባለህ?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስ አጠገብ ቆመው የነበሩትም፣ “የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት ደፍረህ ትሰድባለህን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገቡ የቆሙትም “የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያ የነበሩ ሰዎች ጳውሎስን “የእግዚአብሔርን የካህናት አለቃ ትሳደባለህን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገቡ የቆሙትም፦ የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን? አሉት። |
ጳውሎስም መልሶ፥ “አንተ የተለሰነ ግድግዳ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝዛለህን? እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት ይመታሃል” አለው።
ጳውሎስም፥ “ወንድሞች፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላውቅም መጽሐፍ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር’ ይላልና” አላቸው።