ወደ ዮርዳኖስም እንሂድ፤ ከእኛም እያንዳንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፥ የምናድርበትም ቤት እንሥራ፥” አሉት፤ እርሱም፥ “ሂዱ” አለ።
ሐዋርያት ሥራ 20:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም እጆች ለምሻው ነገርና ከእኔም ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋራ ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገዛ እጆቼ እየሠራሁ ራሴንም ሆነ ጓደኞቼን እረዳ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። |
ወደ ዮርዳኖስም እንሂድ፤ ከእኛም እያንዳንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፥ የምናድርበትም ቤት እንሥራ፥” አሉት፤ እርሱም፥ “ሂዱ” አለ።
ከሚያገለግሉትም ሁለቱን ጢሞቴዎስንና አርስጦስን ወደ መቄዶንያ ላከ፤ እርሱ ራሱ ጳውሎስ ግን ብዙ ቀን በእስያ ተቀመጠ።
ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ የመቄዶንያን ሰዎች የጳውሎስን ወዳጆች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስንም ከእነርሱ ጋር እየጐተቱበአንድነት ወደ ጨዋታው ቦታ ሮጡ።
በድካማችንና በሥራችን ነዳያንን እንቀበላቸው ዘንድ እንደሚገባን ይህን አስተምሬአችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውንም የጌታችንን የኢየሱስን ቃል ዐስቡ።”
በእጃችን ሥራ እያገለገልን እንደክማለን፤ ይረግሙናል፤ እኛ ግን እንመርቃቸዋለን፤ ያሳድዱናል፤ እኛ ግን እንጸልይላቸዋለን፤ እንታገሣቸዋለንም።
ወንድሞች ሆይ! ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋል፤ ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን እየሠራን፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን።