ሐዋርያት ሥራ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ተገረሙ፤ የሚሉትንም አጡ፥ እርስ በርሳቸውም፥ “እንጃ! ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም በአድናቆትና ግራ በመጋባት፣ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሁሉም ተገርመውና የሚሉትን አጥተው “ይህ ነገር ምን ይሆን!” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው፦ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ። |
ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር።
ጴጥሮስም ስለ አየው ራእይ ምን እንደ ሆነ ሲያወጣና ሲያወርድ ከቆርኔሌዎስ ተልከው የመጡ ሰዎች የስምዖንን ቤት እየጠየቁ በደጅ ቁመው ነበር።
ከቀርጤስና ከዐረብም የመጣን፥ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ጌትነት በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።”