La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጴጥ​ሮ​ስ​ንም በወ​ኅኒ ቤት ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ዘወ​ትር ስለ እርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጴጥሮስም በዚህ መሠረት እስር ቤት ተጣለ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ስለ እርሱ አጥብቃ ወደ እግዚአብሔር ትጸልይ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ጴጥሮስ በወህኒ ቤት ተይዞ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር በጥብቅ ትጸልይ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 12:5
12 Referencias Cruzadas  

ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ፥ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።


ዘወ​ትር እን​ዲ​ጸ​ልዩ፥ እን​ዳ​ይ​ሰ​ለ​ቹም በም​ሳሌ ነገ​ራ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ።


ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።


ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር።


አንዱ የአ​ካል ክፍል ቢታ​መም ከእ​ርሱ ጋር የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ይታ​መ​ማሉ፤ አንዱ የአ​ካል ክፍል ደስ ቢለ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


በብ​ዙ​ዎች ጸሎት ጸጋን እና​ገኝ ዘንድ፥ ብዙ​ዎ​ችም በእኛ ፋንታ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ እና​ንተ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ርዱን።


ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።


ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።


እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።