La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደግ​ሞም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጹሕ ያደ​ረ​ገ​ውን አንተ አታ​ር​ክ​ሰው’ የሚል ቃል ከሰ​ማይ መለ​ሰ​ልኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ያም ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ፣ ‘እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ እንደ ርኩስ አትቍጠረው’ ሲል ከሰማይ ተናገረኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁለተኛም ‘እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው፤’ የሚል ድምፅ ከሰማይ መለሰልኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ሁለተኛ ጊዜ፥ ‘እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ ርኩስ ነው ማለት አይገባህም’ የሚል መልስ ከሰማይ ሰማሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለተኛም፦ “እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው” የሚል ድምፅ ከሰማይ መለሰልኝ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 11:9
9 Referencias Cruzadas  

ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ፤” አላቸው።


ዳግ​መ​ኛም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጹሕ ያደ​ረ​ገ​ውን አንተ አታ​ር​ክስ” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።


ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ ሰው ሄዶ ከባ​ዕድ ወገን ጋር መቀ​ላ​ቀል እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ባው ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማን​ንም ቢሆን እን​ዳ​ል​ጸ​የ​ፍና ርኩስ ነው እን​ዳ​ልል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​የኝ።


እን​ዲ​ህም መላ​ልሶ ሦስት ጊዜ ነገ​ረኝ፤ ዳግ​መ​ኛም ሁሉ ተጠ​ቅ​ልሎ ወደ ሰማይ ተመ​ለሰ።


‘አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ንጹሕ ያል​ሆነ ርኩስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያ​ው​ቅም’ አልሁ።


ልባ​ቸ​ው​ንም በእ​ም​ነት አን​ጽቶ ከእኛ አል​ለ​ያ​ቸ​ውም።


በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነውና።