ያመሰግኑት ዘንድ ያለ ጥርጥርም በቀና ልቡና አምልኮቱን ያውቁ ዘንድ፥ ከፈጠራቸውና ከመገባቸው፥ ከአከበራቸውና ከአሳደጋቸው ከእግዚአብሔርም ብቻ በቀር ለሌሎች አማልክት የሚሰግዱ እንዳይሆኑ እርሱ ሰውን በመልኩና በምሳሌው ፈጥሮታልና ልብንና ኵላሊትን ይመረምራል።