የእግዚአብሔርን ምክሩንና ጥበቡን መመርመር የሚችል ማን ነው? እርሱ ምድርን በውኃ ላይ መሥርትዋታልና፥ ያለካስማም አጽንትዋታልና፥ በፍጹም ጥበቡም ሰማይን በነፋስ አጸናው፤ ተባዕታዊውንም ውኃ እንደ ድንኳን ዘረጋው።