የፈጠረህን ዕወቀው፤ ያጸናህና ያዳነህ የእስራኤልን ቅዱስም አትርሳው፤ አንተ መሬት ስትሆን በመልኩና በምሳሌው ፈጥሮሃልና ደስ ይልህ ዘንድ፥ ምድርንም ትቈፍራት ዘንድ በገነት አኖረህ።