ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤
ከማይረባና ትርጕም የለሽ ከሆነ ክርክር ራቅ፤ ምክንያቱም እነዚህ ጠብን እንደሚያስከትሉ ታውቃለህ።
ጠብንም እንደሚያመጡ ታውቃለህና ከሞኝነትና ከከንቱ ንትርክ ራቅ።
ጠብን እንደሚያመጣ ዐውቀህ ከሞኝነትና ከከንቱ ክርክር ራቅ።
ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።
ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።
ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ኀጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፤
ነገር ግን ሞኝነት ካለው ምርመራና ከትውልዶች ታሪክ ከክርክርም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤
በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በአካላችሁ ክፍሎች ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?