La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ተሰሎንቄ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ፣ “እኔ አምላክ ነኝ” እያለ ዐዋጅ ያስነግራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህ የዐመፅ ሰው አማልክት ተብለው ከሚመለኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል፤ “እግዚአብሔር ነኝ” እያለም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንኳ ለመቀመጥ ይደፍራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።

Ver Capítulo



2 ተሰሎንቄ 2:4
13 Referencias Cruzadas  

ግብ​ፃ​ው​ያን ሰዎች እንጂ አም​ላክ አይ​ደ​ሉም፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሥጋ እንጂ መን​ፈስ አይ​ደ​ሉም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰ​ና​ከ​ላል፤ ተረ​ጂ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ ሁሉም በአ​ንድ ላይ ይጠ​ፋሉ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


ሰለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፤


አንተ ሰው ስት​ሆን ለሚ​ገ​ድ​ሉህ ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለ​ህን? ሰው ነህ እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


በዚ​ህም ሳልፍ ‘ለማ​ይ​ታ​ወቅ አም​ላክ’ የሚል ጽሕ​ፈት ያለ​በ​ትን የም​ታ​መ​ል​ኩ​በ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ች​ሁን አየሁ፤ እነሆ፥ እኔ ይህን ሳታ​ውቁ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን እገ​ል​ጽ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


አማ​ል​ክት የሚ​ሉ​አ​ቸው ነገ​ሮች አሉና፤ በሰ​ማ​ይም ቢሆን፥ በም​ድ​ርም ቢሆን፥ ብዙ አማ​ል​ክ​ትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥