የሶርህያ ልጅ አቢሳም ንጉሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን ይረግማል? ልሻገርና ራሱን ልቍረጠው፤”
2 ሳሙኤል 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “የሞተ ውሻ ወደምመስል ወደ እኔ ትመለከት ዘንድ እኔ አገልጋይህ ምንድን ነኝ?” ብሎ ሰገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜምፊቦስቴ ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፣ “እንደ ሞተ ውሻ ለምቈጠር ለእኔ ይህን ያህል የምታደርግልኝ አገልጋይህ ኧረ ማን ነኝ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፊቦሼት ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፥ “እንደ ሞተ ውሻ ለምቆጠር ለእኔ ይህን ያህል የምታደርግልኝ አገልጋይህ ኧረ ማን ነኝ?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መፊቦሼትም በአክብሮት እጅ ነሥቶ “የሞተ ውሻ ልመመስል ለእኔ ለአገልጋይህ ይህን ያኽል ቸርነት የምታደርግልኝ ለምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የሞተ ውሻ ወደምመስል ወደ እኔ የተመለከትህ እኔ ባሪያህ ምንድር ነኝ? ብሎ እጅ ነሣ። |
የሶርህያ ልጅ አቢሳም ንጉሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን ይረግማል? ልሻገርና ራሱን ልቍረጠው፤”
ዳዊትም ጋድን፥ “በሁሉም እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ በሰው እጅ ከምወድቅ ይልቅ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል” አለው።
አበኔርም ኢያቡስቴ እንዲህ ስላለው እጅግ ተቈጣ፤ አበኔርም እንዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም፥ ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኀጢአት ትከስሰኛለህ።
አዛሄልም፥ “ይህን ታላቅ ነገር አደርግ ዘንድ እኔ የሞተ ውሻ አገልጋይህ ምንድን ነኝ?” አለ። ኤልሳዕም፥ “አንተ በሶርያ ላይ ንጉሥ እንድትሆን እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው።
አሁንም በተራራው ላይ ሰው ቆቅን እንደሚሻ የእስራኤል ንጉሥ ነፍሴን ለመሻት ወጥቶአልና ደሜ በእግዚአብሔር ፊት በምድር ላይ አይፍሰስ።”