እርሱም በእኔ በባሪያህ ላይ ክፉ አደረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ በፊትህም ደስ ያሰኘህን አድርግ።
2 ሳሙኤል 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜምፌቡስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ኖረ፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜምፊቦስቴም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፊቦሼትም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሁለቱም እግሮቹ ሽባ የሆኑት መፊቦሼት በንጉሡ ገበታ እየቀረበ በመመገብ የኢየሩሳሌም ነዋሪ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሜምፊቦስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር፥ ሁለት እግሩም ሽባ ነበረ። |
እርሱም በእኔ በባሪያህ ላይ ክፉ አደረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ በፊትህም ደስ ያሰኘህን አድርግ።
ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ።
ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” አለው።
ዳዊትም፥ “ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፤ የአባትህን አባት የሳኦልን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ሁል ጊዜ ከገበታዬ እንጀራን ትበላለህ” አለው።
በወህኒም ውስጥ ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፥ ኢኮንያንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር።