2 ሳሙኤል 3:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ለአበኔር አለቀሰለት፤ እንዲህም አለ፦ “አበኔር ሰነፍ እንደሚሞት ይሞታልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ለአበኔር ይህን የሐዘን እንጕርጕሮ ተቀኘ፤ “አበኔር እንደ ሞኝ ሰው ይሙት? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ለአበኔር ይህን የኀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ለአበኔር ሐዘኑን በቅኔ ሲገልጥ እንዲህ አለ፦ “አበኔር እንደ ሞኝ ሰው ይሙትን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔር ሰነፍ እንደሚሞት ይሞታልን? |
እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህም በሰንሰለት አልተያዙም፤ ማንም እንደ ሰነፍ አልወሰደህም፤ በዐመፃ ልጆችም ፊት ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት።
ኤርምያስም ለንጉሡ ለኢዮስያስ የልቅሶ ግጥም ገጠመለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር፤ ይህም በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በልቅሶ ግጥም ተጽፎአል።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
ይኸውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞሹለታል፤ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች ያሞሹለታል፤ ስለ ግብፅና ስለ ኀይልዋ ሁሉ ያሞሹለታል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።