የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ከፍ ያደርግ ዘንድ መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰዳት።”
2 ሳሙኤል 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያቡስቴም አበኔርን ይፈራው ነበርና ቃልን ይመልስለት ዘንድ አልቻለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያቡስቴም አበኔርን አጥብቆ ፈርቶት ስለ ነበር፣ እንደ ገና አንዲት ቃል እንኳ ሊመልስለት አልደፈረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያቡስቴም አበኔርን ስለ ፈራ ሌላ ቃል ሊመልስለት አልደፈረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያቡስቴም እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፥ ለአበኔር አንድ ቃል እንኳ ሊመልስለት አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያቡስቴም አበኔርን ይፈራው ነበርና አንዳች ይመልስለት ዘንድ አልቻለም። |
የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ከፍ ያደርግ ዘንድ መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰዳት።”
አበኔርም ለዳዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፤ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፤ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ” ብለው በስሙ ይነግሩት ዘንድ መልእክተኞችን ወዲያውኑ ላከለት።