2 ሳሙኤል 24:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፤ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይሁዳም ተዋጊዎች ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም የሕዝቡን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፥ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብም በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፥ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ በውትድርና ለማገልገል ብቃት ያላቸው ሰዎች መኖራቸውንም ለንጉሡ አሳወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፥ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፥ የይሁዳም ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ። |
የይሳኮር ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥