ወደ ጤሮስም ምሽግ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ከነዓናውያንም ከተሞች ሁሉ መጡ፤ በይሁዳም ደቡብ በኩል በቤርሳቤህ ወጡ።
2 ሳሙኤል 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገሪቱም ሁሉ ላይ ተመላልሰው ከዘጠኝ ወርና ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱን ሁሉ ዞረው ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱን ሁሉ ሲዞሩ ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀን በኋላ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት በመላ ሀገሪቱ ሲዘዋወሩ ቈይተው ዘጠኝ ወር ከኻያ ቀን ከሆናቸው በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገሪቱም ሁሉ ላይ ተመላልሰው ከዘጠኝ ወርና ከሀያ ቀን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። |
ወደ ጤሮስም ምሽግ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ከነዓናውያንም ከተሞች ሁሉ መጡ፤ በይሁዳም ደቡብ በኩል በቤርሳቤህ ወጡ።
ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፤ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይሁዳም ተዋጊዎች ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ።