La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 23:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም ልዩ የሆ​ነ​ውን ግብ​ፃዊ ሰው ገደለ፤ ግብ​ፃ​ዊ​ውም በእጁ ዛቢ​ያው እንደ ድል​ድይ ዕን​ጨት የሆነ ጦር ነበ​ረው፤ በና​ያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብጻዊ ገድሏል፤ ግብጻዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብጻዊውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድ ማራኪ ግብፃዊንም ገድሎአል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር ይዞ፥ በናያ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ነበር ወደ እርሱ የሄደው፤ ከግብፃዊውም እጅ የገዛ ጦሩን በመንጠቅ ገደለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም ጦር ይዞ የነበረውን አንድ ኀያል ግብጻዊ ገድሎአል፤ ይኸውም በናያ በእጁ ከበትር በስተቀር ሌላ የጦር መሣሪያ ሳይዝ ወደ ግብጻዊው ቀርቦ የገዛ ጦሩን በመቀማት በዚያው ጦር ግብጻዊውን ገደለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ረጅሙንም ግብጻዊ ሰው ገደለ፥ ግብጻዊው በእጁ ጦር ነበረው፥ በናያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግብጻዊውም እጅ ጦሩን ነቅሎ በገዛ ጦሩ ገደለው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 23:21
5 Referencias Cruzadas  

በቀ​በ​ስ​ሄል የነ​በ​ረው ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ውን የአ​ር​ኤ​ልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ዩም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።


የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ያደ​ረ​ገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ኀያ​ላን ተጠ​ርቶ ነበር።


ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ረጅ​ሙን ግብ​ፃ​ዊ​ውን ሰው ገደለ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ የሸ​ማኔ መጠ​ቅ​ለያ የመ​ሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።


አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው።


ዳዊ​ትም ሮጦ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ላይ ቆመ፤ ሰይ​ፉ​ንም ይዞ ከሰ​ገ​ባው መዘ​ዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ ራሱ​ንም ቈረ​ጠው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዋና​ቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።