የእስራኤልም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እርሱ ተነሥቶ እጁ እስከሚደክምና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ የሞቱትን ለመግፈፍ ብቻ ተመለሱ።
2 ሳሙኤል 23:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን በእርሻው መካከል ቆሞ ጠበቀ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ገደለ፤ እግዚአብሔርም ታላቅ መድኀኒት አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሣማ ግን የቆመበትን ስፍራ አልለቀቀም፤ ጦርነቱንም ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሻማ ግን የቆመበትን ስፍራ አለቀቀም፤ ጦርነቱንም ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያችም ዕለት ጌታ ታላቅ ድልን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻማ ግን በዚያው በማሳው ውስጥ ጸንቶ ቆመ፤ በመከላከልም ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ታላቅ ድልን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን በእርሻው መካከል ቆሞ ጠበቀ፥ ፍልስጥኤማውያንንም ገደለ፥ እግዚአብሔርም ታላቅ መድኃኒት አደረገ። |
የእስራኤልም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እርሱ ተነሥቶ እጁ እስከሚደክምና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ የሞቱትን ለመግፈፍ ብቻ ተመለሱ።
እርሱ ከዳዊት ጋር በፋሶደሚን ነበረ፥ በዚያም ገብስ በሞላበት እርሻ ውስጥ ፍልስጥኤማውያን ለሰልፍ ተሰብስበው ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ።