2 ሳሙኤል 22:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ አልሰማቸውምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለርዳታ ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ ጌታ ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጮኹ፥ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ አልሰማቸውምም። |
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
በጣዖታቸውና ጣቶቻቸው በሠሩአቸው የእጃቸው ሥራዎች አይተማመኑም፤ ለርኵሰታቸውም ዛፎችን አይቈርጡም።
“የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ሽማግሌዎች ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትጠይቁ ዘንድ መጥታችኋልን? እኔ ሕያው ነኝ! አልመልስላችሁም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሳኦልም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም በሕልም አላሚዎች፥ ወይም በነጋሪዎች፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።